ወጋገን ባንክ አ.ማ. ፒክ አፕ ፎርድ(F150) በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ ወጋገን 035/2018
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
ንብረት አስያዥ |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የተሽከርካሪ ዓይነት |
የሰሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
ዘመን |
የነዳጅ አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቀን |
|
|
ቀን |
ሰዓት |
|||||||||||
|
1 |
አቶ ይፍቱስራ ታደሰ |
ተበዳሪው ድርጅት |
ወላይታ ሶዶ |
ፒክ አፕ ፎርድ(F150) |
አአ-02-C47019 |
1FTEX1C8\ 8HFA82528 |
HFA82528 |
2017 |
ናፍታ |
3,500,000.00 |
ሀምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም |
ከጧቱ 3፡00-6:00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
2. የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
3. በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል።
4. የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፡ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ስዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ስዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው:: ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል።
5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
7. ጨረታው የሚካሄደው፡ በባንኩ ዋ/መስሪያ ቤት ህንጻ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።
8. ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
9. ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል:: ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
10. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።
11. ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ።
12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካግኘ በጨረታው አይገደድም።
ወጋገን ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-07-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-07-20 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Wegagen Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T11:32:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.