በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ በነፋስ መውጫ ቅርንጫፍ በመጋዘን የሚገኘውን ሰብል ክሬም ቦለቄ 4552 ኩ/ል እና ነጭ ቦለቄ 429 ኩ/ል በድምሩ 4981 ኩ/ል ሰብል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሰብል ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎህ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተወሰነ በነፋስ መውጫ ቅርንጫፍ በመጋዘን የሚገኘውን ሰብል ሎት 1 ክሬም ቦለቄ 4552 ኩ/ል ሎት 2 ነጭ ቦለቄ 429 ኩ/ል በድምሩ 4981 ኩ/ል ሰብል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር ይችላል -
1. በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
2. ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /2%/ በጎሕ ሁለገብ የዝ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃየተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
4. የግዥው መጠን ከ200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው: እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሊፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት:: ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ ለሚሸጠው ሰብል እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፣
5. ተጫራቾች የሚገዙትን የሰብል ዓይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የሚገልጽ የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ቀርበው በመግዛት ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000561188126 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በሚያሳውቁት የቴሌግራም አድራሻ ማስላክ ይቻላል::
6. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-5 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
7. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት በ5ቀን ዉስጥ ያሸነፉትን ሰብል ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርባቸዋል።
8. አሸናፊው የሚለየው በሎት /በምድብ/ ዋጋ ይሆናል፡፡ ከሎት ውስጥ የአንዱን ዕቃ ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6.30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10 ኛው ቀን መጨረሻ ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
10. ዪኒየኑ ከሚሸጠው ሰብል ውስጥ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው
11. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ።
ማሳሰቢያ:- ነጭ ቦለቄ እና ክሬም ቦለቄ አስገዳጅ ምርት ስለሆኑ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ብቻ የሚጋብዝ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 1336 / 058 141 9927 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ /ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Publishing entity: ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 05, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.