የደቡብ/ምዕ/ኢ/ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የፓራዶ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕ/ኢ/ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የፓራዶ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በ2019 በጀት ዓመት መ/ቤቱ ውል ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለ6 ወራት የሚቆይ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ እየቀረባችሁ የጨረታ ሠነድ በነፃ በመውሰድ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በመጨመር እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።

  • ለውድድር የቀረቡ መስዋወጫ ዕቃዎች ፡-
  • ሎት 1 የፓራዶ መኪና መለዋወጫ ዕቃ
  • ለውድድር የሚያስፈልግ መስፈርቶች ፡-
  • የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው/ያላት
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ያላት
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ወረቀት ያለው/ያላት
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  • የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00 ከንግድ ባንክ የተረጋገጠውን ሲፒኦ/CPO/ወይም ካልተቻለ በጥሬ አካውንት ቁጥር 1000562153563 አስገብቶ እስሊፕ ማቅረብ ግዴታ መሆኑ፤
  • ተጫራች ወይም ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደትን የማይስተጓጉል መሆኑ፤
  • የጨረታ ውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዣ ከውል በኋላ በተቋሙ አካውንት አስገብቶ እስሊፕ ማቅረብ የሚችል መሆኑ፤
  • በጨረታውን አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃውን ለሀዋሳ ሞኤንኮ ድርጅት በራሱ ወጪ በማቅረብ በአውቶ ባለሙያ የጥራት ደረጃውን አስፈትሾ የማስረከብ ግዴታ ያለበት መሆኑን የተረዳ የተረዳች ሲሆን የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ16ኛው ሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ቀኑ ሰንበት ወይም ሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀናት ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፡-

  • ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0473450911/0473450904/0930712270 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  •  የገንዘብ ክፍያ የሚፈፀመው ሀዋሳ ሞኤንኮ የዕቃውን ጥራት አረጋግጦ መረከቡ ከተረጋገጠ በኋላ የሚፈፀም ይሆናል።

የደቡብ/ምዕ/ኢ/ህዝቦች ክልል ምክር ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት
  • Bid bond: 3,000.00 ብር
  • Published: Jul 07, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders