የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሞተር ሣይክሎችን፣ አገልግሎት የማይሰጡ ተሽከርካሪዎችንና በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በወረዳው ውስጥ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ

  • የሞተር ሣይክሎችን፣
  • አገልግሎት የማይሰጡ ተሽከርካሪዎችንና

በወረዳው ውስጥ የሚገኙ

  • ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም፡-

 በጨረታ ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ የመግዣ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታ ውጤቱ በሚመለከተው አካል ከፀደቀ በኃላ ነው፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው የሚገዛውን ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ግብር የተጨማሪ እሴት ታክስ 15 በመቶ ወጪዎች እና ሌሎች ንብረቶችን ለማንሣትና ለማጓጓዝ የሚውጡ ወጪዎችን እና ሌሎችንም ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ወጪዎች በገዥው አካል ይሸፈናል፡፡
  4. የሚሸጡ ንብረቶች የሚገኙበትን ቦታ በተመለከተ አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት፣ አገልግሎት የማይሰጡ የሞተር ሣይክሎች፣ አገልግሎት የማይሰጡ ተሽከረካሪዎች አገልግሎት ሰጥተው የተቀየሩ የመኪና መለዋወጫዎች በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ውስጥ ባሉ ተቋማት በአካል በመገኘት በማየት ጨረታውን መሙላት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ቦታው በሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ተኛ ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ16ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7.  የጨረታ አሸናፊው የሚለየው ከፍተኛ የመግዣ ዋጋ የሞላው ተጫራች ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ከረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሰራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ውድድሩ በነጠላ ከፍተኛ ዋጋ የሞላው የሚመረጥበት ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ስለሚገዙት ንብረት ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል ቢሮ ቁጥር 4 በመገኘት መጠየቅ ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 05 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Publishing entity: Hulet Eju Enese Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: 100,000 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jul 06, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders