ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ. የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ካቦ፣ ፕላስቲክ ገመድ፣ የመኪና መሸፈኛ ሸራ እና የተለያዩ ዎርክ ሾፕ እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/10/2018

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤ ካቦ፤ ፕላስቲክ ገመድ፤ የመኪና መሸፈኛ ሸራ እና የተለያዩ ዎርክ ሾፕ እቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት

1. በዘርፉ የተሰማሩ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።

7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም

8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።

10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ : ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 7ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-2519

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-07-23
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-23 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Geda Transport and Logistics S.C.
  • Buyer address: ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T08:23:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders