የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች (ደብረ ማርቆስ፣ ሚዛን አማን፣ ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ፣ ወላይታ ሶዶ) የሚገኝ ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ክፍት ቦታ በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የአውሮፕላን ነዳጅ ዲፖ ግንባታ እና የነዳጅ አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T624

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶች (ደብረ ማርቆስ፣ ሚዛን አማን፣ ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ፣ ወላይታ ሶዶ) የሚገኝ ለአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ግንባታና ነዳጅ አቅርቦት አገልግሎት የሚሆን ክፍት ቦታ በረጅም ጊዜ የኮንትራት ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

1. ህጋዊና የታደሰ የነዳጅ አቅርቦት ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ታከስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ በኢትዮጵያ በነዳጅና በዘይት አቅርቦት የሶስት ዓመት እና ከዛ በላይ ልምድ ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይሀ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ረቡዕ, ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T624 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ለእያንዳንዱ ቦታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት የሚያገለግል በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት። ከኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴከኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለየብቻ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል ረቡዕ, ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ያዕቆብ መስቀላ : በስልከ ቁጥር፡ +251-11 517-8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል: YaikobM@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-08-05 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ቦታ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T08:25:41.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders