Land lease and real estate
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለድርጅት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
11ኛ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በዳዋ ጨፋ ወረዳ አስተዳደር የወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በወለዲ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የንግድ 5 ፕሎት እና 2625 ካሬ ሜትር እንዲሁም ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 5 ፕሎት 1000 ካሬ ሜትር በአጠቃላይ 10 ቦታዎች እና 3625 ካሬ ሜትር ቦታዎች ለድርጅት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ተጫራቶች -
1. የጨረታውን ሰነድ በወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮ ብር 400.00 አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ50 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፡ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ25/11 /2018 እስከ 04/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ04/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ይሆናል።
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ25/11/2018 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት በወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. በጋራ ተደራጅተው የድርጅት ቦታ ላይ ሰነድ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ተጫራቾች ከሚመለከተው አካል ጋር የወት የጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ይዘው ሲቀርቡ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
9. ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 1፡30 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች የመመልከት ይችላሉ።
10. የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በወለዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ማስታወቂያ ሰሊጃ ላይ መመልከት ይችላሉ።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥሮች 09 13 68 66 88/
09 45 67 12 04/ 09 14 45 67 88
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በኦ/ብ/ዞን/ደ/ጨ/ወረዳ የወስዲ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-08-10 17:00
- Bid opening (note): በ25/11/2018 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ወለዲ ከተማ መሪ ማ/ቤት
- Bid bond: በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 50 በመቶ ያላነሰ
- Bid document price: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 400.00 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 02, 2026)
- Posted at: 2026-08-03T08:19:09.000Z