ኦሮሚያ ባንክ ተሽከርካሪ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተገለፀውን ተሽከርካሪ ባለበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የተሽከርካሪው አይነት፣የሚገኝበት አድራሻ፣የሰሌዳ ቁጥር፣የሞተር ቁጥር እና የሻንሲ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታው ቀን እና ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
||||||
|
የመኪና አይነት |
የሚገኝበት አድራሻ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሰራበት ዘመን |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
||||||
|
1 |
ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ደብል ጋቢና ፒካፕ (ቀረጥ አልከፈለም) |
ሰንጋ ተራ አከባቢ የሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
አአ-03-B23429 |
2020 |
JTEBB7100B012958 |
1HZ-0947459 |
11,500,000 |
ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከ3፡00-4፡00 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት |
ለሁለተኛ ጊዜ |
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ፣ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ፣ማናቸውም ቀረጥና ታክስ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
8. ተሽከርካሪው ከቀረጥና ታክስ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን እስከ ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚፈለግበት ቀረጥና ታክስ ብር 4,732,379.13 ሲሆን የተሽከርካሪው የጨረታ መነሻ ዋጋ ያልተከፈለ ቀረጥና ታክስን አይጨምርም።
9. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረበውን ንብረት (ተሽከርካሪ) በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ወይም በ011-6-59-14-21/08-82 ኦሮሚያ ባንክ ለም ሆቴል ቅርንጫፍ፣ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
11. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-24 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 08, 2026
- Posted at: 2026-07-08T09:11:39.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.