ኮርዳይድ ኢትዮጵያ ያገለገሉ ጎማዎችንና ባትሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸውና ብቁ ተጫራቾች በታሸገ ፖስታ የዋጋ ማቅረቢያቸውን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ጎማዎችና ባትሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 007-008/2026

ኮርዳይድ ኢትዮጵያ ያገለገሉ ጎማዎችንና ባትሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸውና ብቁ ተጫራቾች በታሸገ ፖስታ የዋጋ ማቅረቢያቸውን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።

1.ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎች

.

የዕቃው መግለጫ

ብዛት

መለኪያ

1

ያገለገለ ጎማ 7.50 × 16

76

ቁጥር

2

ያገለገለ ባትሪ (70Ah/75Ah)

10

ቁጥር

2. የተጫራቾች መስፈርቶችና የጨረታ ማቅረቢያ

ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በታሸገ ፖስታ እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ።

አስፈላጊ ማሳሰቢያ: ከፊል ጨረታ (Partial Bid) አይፈቀድም። ተጫራቾች በሁሉም በዝርዝሩ በተጠቀሱ ዕቃዎች ላይ የሚሸፍን አጠቃላይ የዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ አለባቸው።

የጨረታ ማቅረቢያው የሚከተሉትን መረጃዎች ማካተት አለበት፦

  • የተጫራቹ/የድርጅቱ ሙሉ ስም
  • ሙሉ አድራሻና የመገናኛ መረጃ
  • ለሁሉም በዝርዝሩ ለተጠቀሱት ዕቃዎች የቀረበ ጠቅላላ የግዢ ዋጋ (ump Sum)
  • የተጫራቹ ፊርማ

3. የጨረታ ማቅረቢያ ዝርዝሮችና የጨረታ ማስከበሪያ

3.1 የማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን

  • 9 ሐምሌ 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት

የማስረከቢያ አድራሻ

ኮርዳይድኢትዮጵያ ቦሌ፣ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ፣ አቫንቲ ሬስቶራንት አጠገብ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ከተጠቀሰው የመጨረሻ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

3.2 የጨረታ ማስከበሪያ

ሁሉም ተጫራቾች በኮርዳይድ ስም የተዘጋጀ 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር የጥሬ ገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ (Cash Payment Order — CPO) ከጨረታ ማቅረቢያቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።

የሚያስፈልገውን CPO ያላካተቱ ጨረታዎች ምላሽ ሰጪ ተብለው አይቆጠሩም፤ ስለዚህም ውድቅ ይደረጋሉ።

4. የዕቃዎች ምርመራ

ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ዕቃዎቹን በኮርዳይድ ኢትዮጵያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚከተሉት የሥራ ሰዓቶች መመልከት ይችላሉ፦

  • ሰኞ—ሐሙስ፡ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት
  • ዓርብ፡ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት

5. አጠቃላይ ሁኔታዎች

  • ዕቃዎቹ “እንዳሉ እና ባሉበት” (As-ls, Where-ls) ሁኔታ ይሸጣሉ፤ ኮርዳይድ ኢትዮጵያ ስለ ዕቃዎቹ ሁኔታ ወይም ለአገልግሎት ተስማሚነታቸው ምንም ዓይነት ዋስትና አይሰጥም።
  • ኮርዳይድ ኢትዮጵያ ማንኛውንም ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ መብት ያለው ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት የመስጠት ወይም ለተጫራቾች ተጠያቂ የመሆን ግዴታ የለበትም።
  • አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ የመውሰድና የማጓጓዝ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ።
  • አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነት ማሳወቂያ ከደረሰው በኋላ በአምስት (5) የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን መፈጸም አለበት።

ኮርዳይድ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-16
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-07-16 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Cordaid Ethiopia
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ) ብር
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T11:32:40.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders