የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል የከተማ ግብርና እና የጨርቃ ጨርቅ ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች፣ አላቂ የጋርመንት ዕቃዎች፣ ፍራሽ እንዲሁም ቋሚ የህክምና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ለ/ቤ/ተ/ክ/ማ/ማ 02(001-04/2018)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል Building Reslirt Ftures በሚል ፕሮጀክት ከGPAC በተገኘው ድጋፍ የከተማ ግብርና እና የጨርቃ ጨርቅ ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች አላቂ የጋርመንት ዕቃዎች ፍራሽ እንዲሁም ቋሚ የህክምና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
ደንብ ልብስ |
50,000.00 |
|
ሎት 2 |
አላቂ የጋርመንት ዕቃዎች |
50,000.00 |
|
ሎት 3 |
A-የከተማ ግብርና እና የጨርቃ ጨርቅ ቋሚ ዕቃዎች እንዲሁም |
200,000.00
|
|
|
B-የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች |
|
|
ሎት 4 |
ቋሚ የህክምና ዕቃዎች |
50,000.00 |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ድርጅቱ ያሸነፈውን ጠቅላላውን ዕቃና ግብዓት በአንድ ወር ማቅረብ የሚችል።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000640967181 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከማዕከሉ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ማዕከሉ ባወጣው በስፔስፊክሽኑ መሰረት ብቻ በማድረግ ቫትን ጨምሮ ሞልተው በሰም አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
10. ተጫራቾች አላቂ ዕቃዎች ግብዓት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ወይም ቢድቦንድ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ
ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የገዥ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡-011 143 78666
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-07-21
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Lnegewa Setoch Rehabilitation Center
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 09, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.