የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሊፍት supply and fix በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የሊፍት supply and fix ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ ዲ/ግ/ማ / ድ / ግ / ጨ/ቁ 27/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ሊፍት supply and fix በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 400,000.00 ብር (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (un conditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር ፡-09-20-11-75-60
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
- Bid bond: 400,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 09, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.