Lifts, escalators and conveying systems
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ለጋሻ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል passenger elevator /Lift/ እና supply and fix Roof water tanks አቅርቦት እና ገጠማ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር መሰፋ/ብ/ግ/ጨ/ 01/2018/19
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለሚያስገነባቸው የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ለጋሻ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለፁትን አቅርቦት እና ገጠማ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፤-passenger elevator /Lift/
- ሎት 2፤-supply and fix Roof water tanks
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ VAT Registration Certificate/ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርተፊኬት የብቃት ሰርተፊኬት Tax clearance certificate የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2 ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መ/ሰ/ፋ ግዥ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም ሎት (1) ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ሎት (2) ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
4.. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው::
5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከቀኑ 8፡30 መሰፋ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል፡፡
7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115 572 752
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስዳው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
መከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 14:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Force Foundation
- Buyer address: ከደንበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት ጫካ ቡና አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 03, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T10:42:34.000Z