የኦሮሚያ ፖሊስ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ አባሎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ፣ የአትክልት ሾርባ ባለ 240 ግራም እና የስጋ እስቃጥላ ባለ 240 ግራም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል

Description

በኦሮሚያ ፖሊስ የተዘጋጀ አስቸኳይ
ግ/ጨ/01/29 የበጀት ዓመት

የኦሮሚያ ፖሊስ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ አባሎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ የአትክልት ሾርባ ባለ 240 ግራም፣ የስጋ እስቃጥላ ባለ 240ግራም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-

  • ሎት አንድ፡- ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ
  • ሎት ሁለት:- 1. የአትክልት ሾርባ ባለ 240ግራም 2. የስጋ እስቃጥላ ባለ 240ግራም

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4. ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚወዳደርበት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

5. ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስይዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. የጨረታ ስነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ የማጓጓዣ፣ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ እና ሲያስገባ የየሎቱን ሰነድ ለየብቻ ማቅረብ አለበት። የተለያዩ ሎት በአንድ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ሳጥን የሚያስገባ ድርጅት (ተወዳዳሪ) ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

10. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ቫት እና ማንኛውንም ወጪን ጨምሮ መሙላት አለበት። ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበ ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 15/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።

12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15/11/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ግዥ አገልግሎት መምሪያ ውስጥ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

13. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 የኦሮሚያ ፖሊስ፡-

አድራሻ፡-ኦሮሚያ ፖሊስ አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አካባቢ
ለተጨማሪ መረጃ፡-09 13 10 89 90 ወይም 09 96 05 47 78 መደወል ይችላሉ።
የኦሮሚያ ፖሊስ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Publishing entity: Oromia Police Commission
  • Bid bond: 2% ሆኖ የሚያስይዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jul 09, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders