በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓም
በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት ለዞን ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ለ6 ወራት የሚቆይ
- በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች
- ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች
- የልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች የጌጣጌጥ /የዲኮር/ ዕቃዎች 6 ወራት የሚቆይ
- ለተለያዩ ተሸከርካሪዎች ዘይትና ቅባቶችን
በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፤የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማለትም በተራ ቁ1 ለተገለፀው ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/ በተ.ቁ.2 ለተገለፀዉ ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ በተራ.ቁ 3 ለተገለፀዉ ብር 130,000.00 /አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር/ በተራ.ቁ. 4 ለተገለፀዉ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በተራ.ቁ.5 ለተገለጸው ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በምርጫቸዉ በአንዱ ከዋናዉ /orignal የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ02/11/2018 ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ማለትም 16/11/2018 11፡30 ሰዓት ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 2- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ 02/11/ 2018 ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ማለትም እስከ 16/11/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል ፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል።
- ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ጨረታውን በነጠላ ዋጋ የሚያወዳድር መሆኑን እናሳዉቃለን።
- የጨረታ ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
በአብክመ የኦሮሞ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ
ትብብር መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Publishing entity: ANRS Oromo Zone Finance Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 09, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.