በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የመኪና ጎማ እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የመኪና ጎማና መለዋወጫዎች ግዥ ብሄራዊ

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማ እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት 2 የመኪና ጎማ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ

  1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፣ግዥው ከ200,000 በላይ የሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስት /16/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በቀን 20/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ላይ በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5.  ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
    • ሎት 1. 25,000 ብር /ሃያ አምስት ሺህ ብር
    • ሎት 2. 25,000 ብር /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
  6. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርበታል።
  7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-27
  • Publishing entity: Kemise City Administration Finance and Economic Cooperative Bureau
  • Bid bond: 25,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jul 10, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders