የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ ዘሪሁን ሙላቱ የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሠረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል

..

 

የንብረቱ ዝርዝር

 

ብዛት በቁጥር

የጨረታው መነሻ ዋጋ

የንብረቱ ሁኔታ

የጨረታው ሁኔታ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

Baking Rotary Oven with Burner

  • Brand: ALTUNTOP, Model: ATDF-250, Trolley capacity 16shelves, Origin: Turkey

1

9,792,345.08

 

አዲስ

 

ድርድር ጨረታ

 

ሐምሌ 30 ቀን 2018 .. ጠዋት 400 እስከ 600 ሰዓት

 

2

Mixer፡

  • Brand: ALTUNTOP, Model: ATSM120,Flour capacity - 75Kg, Origin: Turkey

1

3

Dough Divider

  • Brand: ALTUNTOP, Model - ATK60T, Origin: Turkey

1

4

Dough Moulder Machine

  • Brand: ALTUNTOP, Model: ATF2, Origin: Turkey

1

5

Proofer with Steam Generator

  • Brand: ALTUNTOP, Model: ATPC, Origin: Turkey

1

6

Trolley with 16 tray

  • Brand: ALTUNTOP
  • Pan Dimension – 80x100
  • Number of pans per trolley - 16
  • Material - Aluminium

4

7

Bread Slicer

  • Brand: ALTUNTOP, Model: ATED, Origin: Turkey

1

8

Sound Proof Generator

  • Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 30KVA

1

የድርድር ጨረታው መመሪያ

1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር1,958,469.02 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይጠበቅበታል። ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻውን ማስገባት ይችላል።

2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፣መናኸሪያ ክ/ከተማ፣ጉዊ ቀበሌ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው።

3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ/ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፣

3.1 የንብረቱ የሸያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።

3.2 ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ማቅረብ ያስፈልጋል ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈልገውን የጉሙሩክ ቀረጥና ታክስ መክፈል ግዴታ አለበት።

4. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል። የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣

5. ንብረቱን በባንኩ ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።

6. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ከፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት።

7. የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣ መትከያ፣ ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል።

8. የድርድር ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን ቢሮ ውስጥ ይደረጋል።

9. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 27 89 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

10. ንብረቱን ለመጎበኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Bid bond: (20%) ብር 1,958,469.02 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም)
  • Published: Jul 12, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders