ሕብረት ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።

.

የቅርንጫፍ ስም

የተበዳሪ   ስም

የአስያዥ ስም

የሰሌዳ ቁጥር

የተሽከርካሪ አይነት

የስሪት አመት

የሻንሲ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1.

በቅሎ ቤት

ስማያዝ ትራንስአክት ኢንተርናሽል /የተ/የግ/ማህበር

ወይ. ፌቨን አየለ በላቸው

አአ-02-01-A36603

 ኒሳን ጁክ

2012 ..

JN8BF55S4CT012318

HR16*242892C*

1,739,130.44

ሐምሌ 24 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

2.

መሃል አራዳ

አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ

አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ

ኢት-03-01-69784

የደረቅ ጭነት (IVECO)

2014 ..

WJM3TRE9FC304087

F3BEE681G*B220-232930*

10,000,000.00

ሐምሌ 27 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

3.

መሃል አራዳ

አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ

አቶ ተሾመ አንተነህ አለምነህ

ኢት-03-24286

ተሳቢ (ደረቅ ጭነት)

2016 ..

   CT-4160-15

       –

2,000,000.00

ሐምሌ 27 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት


የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል።
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
  4. በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው ንበረት ሐራጁ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ በተ.ቁ 2 እና 3 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚከናወነው ባህርዳር ከተማ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ነው።
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
  7. ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ እስከ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
  8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸዉ በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር የጨረታዉ አሸናፊ (ገዥዉ) ይከፍላል።
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ መረጃ ብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114706380/0114666593 እና ባህርዳር ዲስትሪክት 0583204232 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Publishing entity: Hibret Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 12, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders