አደይ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት (ከሐምሌ 1,2017 እስከ ሰኔ 30,2018) ድረስ ላለው ጊዜ ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል
Description
የውጭ ኦዲተር ጨረታ ማስታወቂያ
አደይ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በአንቀጽ (57) በንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ሐምሌ 23/2016 ዓ/ም የተመሰረተ እና በመዝገብ ቁጥር 7345 የተመዘገበ እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ህጋዊ ሰውነት የተሠጠው ሲሆን መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሀገር በቀለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዋና ዋና አላማዎች መካከል፡-
- በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ከቤት ንብረታቸውና ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለሚፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ኢትዮጵያዊያንን እና የአለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችን በማስተባበር በጊዜያዊነትና በቋሚነት መልሶ ማቋቋም ሥራን ለማከናወን ሲሆን።
- በልዩ ልዩ ችግር ምክንያት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ለህብረተሰብ ክፍሎች ለአረጋዊያንና ለአቅመደካሞች የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ሲሆን
- ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ያጡ ህፃናት በማሰባሰብ የህፃናት ማዕከል በማቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ድጋፎችን የሚደረግ እና ብቁ አገር ተረካቢ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያደርግ ሲሆን
- የጤና ተቋማትን ግንባታና እድሳት፣ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እና የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን
- የትምህርት ቤት ግንባታና እድሳት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፎችን የሚያደርግ ሲሆን በዚህም መሰረት ነው።
(ከሐምሌ 1,2017 እስከ ሰኔ 30,2018) ድረስ ላለው ጊዜ ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል።
ስለሆነም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎችንና የተፈቀደላቸው ኦዲተሮችን አወዳድሮ ሂሳቡን ማስመርመር ይፈልጋል
መስፈርቶች
- የኦዲተር የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገበበት/የተመዘገበችበት
- የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ያላት
- በSAS የሂሳብ ምርመራ ልምድ ያለው/ያላት
አመልካቾች በሚያመለክቱበት ወቅት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ (TOR) ብር 100 በመክፈል መግዛትና የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛል አዘጋጅተው ማቅረብ አለባቸው
- የማመልከቻ ጊዜ ከሐምሌ 6/2018- ሐምሌ 11/2018
- የጨረታ ሰነዱን የማስረከቢያ ጊዜ ሐምሌ 13-15/2018 ጉርድ ሾላ ከቴሌው ወደ መናኸሪያው ሲወጡ ትርስሴት ክሊኒክ አጠገብ ያለው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-35-42-67-54 (09-35-48-81-45) በመደወል መጠየቅ ይቻላል
አደይ የአለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት
ስልክ፡-251-935426754
Email:- adaybagoadragot@gmail.com
Telegram https://t.me/adeycharitableorg ADH
Tender details
- Deadline: 2026-07-22
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-22 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Adey International Charitable Organization
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jul 12, 2026
- Posted at: 2026-07-13T10:18:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.