አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር የኤክስፖርት ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
Doc No.:OF/ATH/030
የጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር የኤክስፖርት ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የዚህን ጨረታ ሰነድ በተገለፀው አድራሻ በመግዛት ማንኛውም ተወዳድሮ ያሸነፈው አካል እቃዎቹን መግዛት የሚችል ሲሆን:-
1. የጨረታ አይነት፡- የጨረታ ሸቀጦቹ አይነት ደግሞ የሰሊጥ ተረፈ ምርት: የማሾ ተረፈ ምርት ና የቦለቄ ተረፈ ምርት እንዲሁም እጣን ናቸው። ኩባንያችን እነዚህን ሸቀጦች አደራጅቶ ገዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ነው፤
2. ማንኛውም ተጫራች (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው) በአንድ የጨረታ አይነት ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ገዝቶና ሞልቶ ማስገባት አይችልም። ሆኖም ሻጭ ለሽያጭ ባወጣቸው የተለያዩ አይነት ተረፈ ምርቶች ላይ በሁሉም ላይ በመሳተፍ ዋጋ ማቅረብ ይችላል። እያንዳንዱ ተጫራች በተመሳሳይ ጨረታ አይነት ላይ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረቡ ከተረጋገጠ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
3. ሻጭ ይህንን ጨረታ ሰነድ በመሸጡ ምክንያት በማንኛውም ሁኔታ የውል ስምምነት እንዲፈጽም አያስገድደውም:: የውል ስምምነት እንደያዘም አይቆጠርም።
4. ተጫራቾች ለመግዛት ዋጋ የሰጡበትን የተረፈ ምርት አይነት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በኩባንያው ዋና መ/ቤት ወይም በሁሉም ቅርንጫፍ መጋዘኖች ለሽያጭ የቀረቡትን ተረፈ ምርቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመግዛት መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአቅራቢያው በሚገኘው ሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503; ባህር ዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኘው አምባሰል ህንጻ 1ኛ ፎቅ ደሴ መናሃሪያ ጀርባ ከሚገኘው እህል ንግድ ፊት ለፊት አምባሰል የሚገለገልበት ቢሮ ወይም ጎንደር ከተማ ከሚገኘው የኩባንያው ጎንደር ሰሊጥ ማቀነባበሪያ አገልግሎት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ቢሮ ፣በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ዜጋ ለመሆናቸው ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ፓስ ፖርት ኮፒ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ከሆኑ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
7. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት እለት 05/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን የጨረታው የአየር ግዜ ቆይታ ሲጠናቀቅ ማለትም በ22/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል። የኩባንያው ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ የጨረታ ሰነድ ከቅርንጫፍ መ/ቤቶች የሚመጣበትን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ማለትም በ25/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503 የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታ መክፈት ስነ-ስርዓቱ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም።
8. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚያወጡት የትኛውም ዓይነት ወጭ (በጨረታው ተሳትፎ ቢያሸንፍ፣ ቢሸነፍ፣ በተለያየ ምክንያት ከጨረታው ውጭ ቢደረግ ወይም ጨረታው ቢሰረዝ) ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።
9. በጨረታ ሰነዶቹ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ተጫራች በዚህ የጨረታ ሰነድ ላይ በተመለከተው የሻጭ አድራሻ የሚፈልገውን ማብራሪያ በፅሑፍ መጠየቅ ይችላል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ያለባቸው ከሻጭ ብቻ ነው:: ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዱን በቀጥታ ከሻጭ ካለማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ወይም አለመሟላት ሻጩ ተጠያቂ አይሆንም።
11. ሻጭ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
ስልክ ቁጥር 011 470 1748 / 09 35 42 96 58
Tender details
- Deadline: 2026-07-29
- Publishing entity: አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 12, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.