አቢሲንያ ባንክ አ/ማ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ/ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንሎች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ተሽከርካሪዎቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተስርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ስዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊተጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፦ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱት ተሸከርካሪዎች ተነጣጥለው አይሸጡም፤ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለየብቻ መሰራት አለበት።
በተ/ቁ. 3 ላይ የተጠቀሰዉ ተሸከርካሪ ቀረጥ አልተከፈለበትም።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሸከርካሪው ዓይነት እና የተሰራበት ዘመን |
የተሸከርካሪው ሞዴል
|
የሻንሲ ቁጥር
|
የሞተር ቁጥር
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
|
1 |
አቶ ሶፎንያስ ስማቸው ጥሩዬ |
ተበዳሪው |
ኢት-03-A33509 |
የጭነት፣ 2021
|
ZZ1257N4341W
|
LZZ5BLSF6MW808858
|
WD615.47*210807018027 |
10,230,000.00
|
ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
|
2 |
አቶ ሶፎንያስ ስማቸው ጥሩዬ |
ተበዳሪው |
ኢት-03-40136
|
ተሳቢ፣ 2025
|
HABTOMG/EHZABEIR
|
EBHBDAHGEP0000088
|
…. |
4,812,060.00
|
|||
|
3 |
አቶ ይበልጣል ሙሉጌታ ሰሜ |
ተበዳሪው |
ኢት-03-A35256
|
የጭነት፣ 2025
|
ZZ3257N3447A |
LZZ5ELNB2SN302883
|
WP10340E221624K066194
|
10,042,560.00
|
ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30-10:00 |
|
4 |
ቤቴል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
አአ-03-B19902 |
ሕንድ/2020 ሱዙኪ ኬሪ ቫን ተሸከርካሪ |
CARRY1.2(AJ3412)
|
MA3EDA53T00170023
|
G12BN809486
|
1,874,250.00
|
ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30_10:00
|
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 12, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.