ዓባይ ባንክ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ዓባይ ባንክ አ.ማ
ያገለገሉ እቃዎች  ሽያጭ ጨረታ – ማስታወቂያ ቁጥር ዓባይ 01- 2026-27

ዓባይ ባንክ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት እቃዎች በጨረታው የተጠቀሱ ቅድመ ሁኔታዎችን በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ።

.

የእቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን

1

የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸሮች

በጥቅል

በጥቅል

75,000

2

ኮምፒውተር

በቁጥር

133

100,000

ሲስተም ዩኒት/ሞኒተር

በቁጥር

129

25,000

3

ዩፒኤስ (UPS)Power Stabilizer

በጥቅል

በጥቅል

5,000

4

ፕሪንተር

በቁጥር

112

25,000

5

ፋክስ ማሽን

በቁጥር

11

5,000

6

ፎቶ ኮፒ ማሽን

በቁጥር

47

10,000

7

ስካነር፣ ካሜራ ስካነር እና ቼክ ስካነር

በጥቅል

በጥቅል

5,000

8

የብር መቁጠሪያ ማሽን

በጥቅል

በጥቅል

5,000

9

ጄነሬተር

በቁጥር

22

7,000 (ለአንድ ጄነሬተር)

10

የጥበቃ ቤት

በቁጥር

25

100,000

11

የተለያዩ እቃዎች፡- የኤሌትሪካል ካልኩሌተር፣ ቡሎር ማሽን፣ ቬንትሌሽን ፋን፣ የውሃ ማጣሪያ እና የመሳሰሉት

በጥቅል

በጥቅል

5,000

12

የተለያዩ እቃዎች፡-  ፋይል ካቢኔት፣አልሙኒየም ፓርቲሺን እና በር፣ካውንተር እና ዲክስን ሴልፋ

በጥቅል

በጥቅል

10,000

13

የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪ እና የመኪና መለዋወጫ

በጥቅል

በጥቅል

5,000


1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በዓባይ ባንክ ዓብይ ቅርንጫፍ በመክፈልና ደረሰኙን በመያዝ ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00- 6፡00፣ ከስዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ማግኘት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዕቃዎች ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. በተራ ቁጥር 2 ላይ ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች (Desktop Computer) የባንኩ መረጃ ለመጠበቅ ሲባል ሃርድ ድራይቨ እና ራም (Hard Drive እና RAM) ከዕቃዎቹ ላይ በማውጣት ለጨረታ የቀረቡ ናቸው።

4. ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) በሰንጠረዥ በቀረበው የብር መጠን መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፋያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል።

8. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ10/አስር/ቀናት ውስጥ ከፍሎ ንብረቶችን ከመጋዘን ላይ ማንሳት ይኖርበታል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-11 557 1529/+251-11 554 9741 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
“ዓባይ- የታላቅነት  ምንጭ!”


Tender details

  • Deadline: 2026-07-27
  • Publishing entity: Abay Bank
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jul 12, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders