ጉሌ ውሃና ኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረትነታቸው የድርጅቱ የሆኑ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር ጉ.ዉ.ኮ.ድ 29/09/2018
ጉሌ ውሃን ኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረትነታቸው የድርጅቱ የሆኑተ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል።
2. ተጫራቾች ፒያሳ በሚገኘዉ ቢሮኣችን በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ቅዳሜም ጨምሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።
5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ዉጭ ይደረጋል።
6. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ይሆናል።
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡10 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፒያሳ በሚገኘዉ ብሮዋችን መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ላይ ቢዉልም ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ላይ ከዋለ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም።
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል።
9. ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል ማሰከበረያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ያለበት ሲሆን ክፍያዉ ፍጽሞ ካጠናቀቀ በኋላ ያሰያዘዉ የዉል ማሰከበሪያ ተመላሽ ይሆማል።
11. ድርጅቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 13 45 62 58 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ
ለሽያጭ የቀረቡ ተሸከርካሪዎች ዝርዝር
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪዉ ዓይነት |
|
1 |
ዳዎ ገልባጭ መኪና Daewoo Truck |
|
2 |
ዳዎ ገልባጭ መኪ / Daewoo Truck |
|
3 |
ባለጎማ ሎደር /wheel |oader/ |
|
4 |
ባለጎማ ሎደር /wheel loader/ |
ጉሌ ውሃና ኮንስትራክሽን ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-08-03
- Publishing entity: Gulle Water Construction Enterprise
- Bid bond: 5% ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ
- Bid document price: 700.00 ብር
- Published: Jul 14, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.