በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተዉ ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-01/2019

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም

  • AC ADAPTOR HD TV CABLE FOLDABLE KID MINI LAPTOP TABLE TV WALL MOUNT LED HIGHBAY LIGHT SKMEI IRON ADULT HAND WATCH WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND: LED STRING LIGHTS:
  • RUBBER NAIL FILTER, S/S MANICURE,  METAL DECORATIVE & EYE LASH PHOTO COPY MACHINENERY AND PRINTER ADULT FABRIC CAP, SHOPPING BAG & OTHERS RECHARGEBLE CAMPING PORTABLE SHOWER:
  • WALL TRANSFORMER CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEL PIPE! HEALD FRAME: FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWEL WIRE PROFESSIONAL HOTEL SPECFLC  TELEPHONE RELIGIOUS BOOKS COMPLET SET DOUBLE LEAF SIEEL FRE RAED DOOR
  • የተለያዩ የህክምና መገልገያ እቃዎች፣
  • SNGLF DOUBLF PORI FACE PLATE & OTHER S/S ARTIFICIAL EARRING & BEARING, SCHOOL BAG & FABBIG ADULT CAP LABORADORY STOOL CHAR እና
  • የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማዎችና ሌሎች እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ረፋዱ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀነ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይቻላል።

2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3) ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MODJO BRANCHOFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።

4) የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10) ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን

ሞጆ  ጉምሩክ  ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-20
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Published: Jul 14, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders