ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኋ/የተ/የግ/ማህበር የህክምና መድኃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሪኤጀንት እና ኬሚካሎችን አመታዊ ግዥ ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ Medx/TND/2018-001

የፕሮጀክቱ ስም፡ የህክምና መድኃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሪኤጀንት እና ኬሚካሎችን አመታዊ ግዥ

ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኋ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል መንግስት የበጀት ድጋፍ የተቋቋመ እና በክልሉ የልማት ድርጅቶች ማዕቀፍ ስር የሚገኝ ሲሆን በጤና አገልግሎት እና ምርት ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የህክምና መድኃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ሪኤጀንት እና ኬሚካሎችን በሶስት ማሰራጫ ጣቢያዎች ባህርዳር፣ ደሴ እና ጎንደር ክላስተሮች ለሚገኙ ጤና ተቋማት በማቅረብ ይታወቃል:: ይህን ተግባር ለመወጣት በ2019 ዓ.ም ለ አንድ (1) ዓመት ለሚቆይ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አምራች ፋብሪካዎች፣ ኢንተርናሽናል ድርጅቶች ህጋዊ እውቅና ካላቸው አስመጭዎች (Importers) ጋር በጨረታ ህግ መሰረት ውል ይዞ መስራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ህጋዊ መስፈርቶችና በሰነዳቸው ላይ የሚያያይዙ ቅድመ ብቃት ማረጋገጫዎች፡-

  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው፤
  • የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የታክስ ክሊራንስ (Tax clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በኢትዮጵያ የምግብና መድኋኒት ቁጥጥር ባለስልጣን (EFDA) በ2018 ዓ.ም ያገኙትን የሙያ ፍቃድ ወይም የብቁ አምራችነት /Good manufacturing practice-GMP/ የብቃት Certificate ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የአንድ መድኃኒት ጀነሪክ ስም ፣ አዘገጃጀት (preparation)፣ የዶዝ (Strength in mg) በግልፅ በተመለከተው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ነጠላ ዋጋ (unit cost) መሙላት ይኖርባቸዋል።
  • የመወዳደሪያ ዋጋው ቫት እና ሌሎች የታክስ ወጭዎችን ሁሉ ያካተተ መሆን አለበት።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እና የሚያቀርቡት መድኃኒት አገልግሎት ዘመኑ 1 ዓመት ከስድስት ወር ያነሰ መሆን የለበትም (>1 year 6/12 month)
  • አቅራቢዎች ላቀረቡት ምርት የጥራት ችግር (Defect) እንዳለ በEFDA ሲረጋገጥ እስከ ሁለት ዓመት ኃላፊነት ሊወስዱ ይችላል።

2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በተመለከተ፡-

  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ CPO ወይም ኦሪጅናል unconditional bank guarantee 200,000.00 ሁለት መቶ ሽህ ብር የጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች ላሸነፉት Item በውሉ ዘመን የሚቆይ የባንክ CPO ወይም ጋራንቲ 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) እንዲያስይዙ ይጠበቃል።
  • ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሽያል ምላሻቸውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ሲኖርባቸው CPO ከፋይናንስ/ዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብሮ ይታሸጋል።
  • አሸናፊው ድርጅት እንዲያቀርብ ታዝዞ ባለመፈፀሙ የቃል ማስጠንቀቂያ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ማስጠንቀቂያ እና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በሚል ሶስት ጊዜ ከተሰጠው በኋላ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ይወረሳል።

3. ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ጊዜ፡

  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሚዲክስ ዲያግኖስቲክስ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 30/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ዕለት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የአሸነፉትን መድኃኒት አይነት ርክክብ በተመለከተ በአዲስ አበባ በሜዴክስ እስቶር የሚከናወን ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የሚገዛቸው የመድኃኒቶች መጠን በተቋማት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እና እንድናቀርብ ስንጠየቅ ግዥ የምንፈፅም እንጅ ለእያንዳዱ Items ከመነሻው የተወሰነ እና የተገደበ መጠን (quantity) አይኖረውም።

  • ለበለጠ መረጃ ባህርዳር ሬስ ኢንጅነሪግ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 6668 / 0947 050 435 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  • አሸናፊ ድርጅቶች ስለሚያቀርቡት መድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አይነት እና መጠን ከ 2 ወር በፊት ቅድመ ጥያቄ የሚቀርብላቸው ሲሆን በዚሁ ጊዜ ውሰጥ (ከተጠየቁ ጀምሮ ባለው 2 ወር ውስጥ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ከአሸናፊዎች ጋር የሚያዘው ውል እና የመወዳደሪያ ዋጋ ለ አንድ (1) ዓመት የሚቆይ ሲሆን ከመስከረም 1/2019 ዓ.ም እስከ ነሃሴ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ድርጅቱ ለተጨማሪ አንድ(1) ዓመት ሊያራዝም ይችላል።
  • የሚገዙ የመድኋኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  • ከአሁን በፊት በነበሩ በሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ባወጣቸው ጨረታዎች ላይ ቀርበው ውል ባለመፈፀም ምክንያት የተቀጡ ድርጅቶች በዚህ ጨረታ ላይ የማይሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
  • በፖስታ የሚላክ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ድርጅቱ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Publishing entity: Medex Diagnostics PLC
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders