ሲንቄ ባንክ አ.ማ. መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር ሲባ/ህአዲ/ሐራጅ/035/2018
ሲንቄ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበዉ ንብረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
|
ጨረታው የሚከናወንበት |
ጨረታው የወጣው |
|||
|
|
|
|
ቀን |
ሰዓት |
|
|||||
|
1
|
ጌትነት መገርሳ ጪብሳ |
ጌትነት መገርሳ ጪብሳ |
ኦዳ |
ሱዙኪ እስዊፍት ሞዴል 2022 |
AA-02-C29379 |
MBHCZC63S00B41169 |
1,824,000 |
24/11/2018 |
4፡30-5፡30 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
የሐራጁ ደንቦች፤
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ/ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካል ከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
- በሐራጁ ሂዳት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ማን እንደሆነ ብቻ የሚገለፅ ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ሰው/አካል ስለማሸነፉ በሚመለከተው የባንኩ አካል ከተረጋገጠ በኃላ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጠዋል።
- ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
- ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፤ ካዛንቺስ የምገኘዉ ሲንቄ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ይሆናል።
- በጨረታዉ ቀን ከ4፡30 እስከ 5፡00 የተጨራቾች ምዝገባ ሰዓት ሲሆን፣ ከ5፡00 ሰዓት በኋላ የተጫራች ምዝገባ አይኖርም። ከ5፡00 – 5፡30 ሐራጁ የሚካሄድበት ጊዜ ይሆናል።
- ለስም ዝውውር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከታክስ እና ግብር ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል።
- የንግድ ማህበራትን በመወከል መጫረት የሚፈልግ ማንኛዉም ግለሰብ የማህበሩን ህጋዊ ሰዉነት ያለዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ወይም እና የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህጋዊ የዉክልና ስልጣን ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለሐራጅ የቀረበ ንብረትን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከአበዳሪ ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
- ተጫራች የጨረታ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰዉ ነዉ።
- ለተጨማሪ መረጃ የሲንቄ ባንክ ህግ አገልግሎት ክፍል ስልክ ቁጥር (+251-11 557-6016), ፤ ኦዳ ቅርንጫፍ (011 557 1965) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሲንቄ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Publishing entity: Siinqee Bank Share Company
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 15, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.