ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግል ማህበር ለመንገድ እና ለተለያዩ ሆስፒታሎች የጽዳት ሥራ አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ ዕቃዎችን ግዢ እና አገልግሎት ግዢ ለማከናወን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/39/2018

የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለመንገድ እና ለተለያዩ ሆስፒታሎች የጽዳት ሥራ አገልግሎት ግብዓት የሚሆኑ ዕቃዎችን ግዢ እና አገልግሎት ግዢ ለማከናወን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል።

በዚህም 

  • ሎት1፡- የሰራተኞች ሰርቪስ መኪና ኪራይ እና የቦቴ መኪና ኪራይ እና ውኃ አቅርቦት 
  • ሎት2፡- የመንገድ እና ለተለያዩ ሆስፒታሎች የጽዳት ሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ አንጸባራቂ ጃኬቶች፣ አንጸባራቂ ሰደርያዎች፣ ጋሪ፣ የቆዳ ጓንት፣ የጨርቅ ማስክ፣ መንገድ በጽዳት ላይ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት፣ ጎግል መነጽር፣ አካፋ፣ የሰሌን ባርኔጣ ወዘተ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-156 9992
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-28 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000958158
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jul 16, 2026
  • Posted at: 2026-07-16T07:53:19.000Z
  • Buyer website: https://commercialnominees.com/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders