በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ_02/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸዉን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩከ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ የስቴሽነሪና የማስታወቂያ ዕቃዎች CONNECTING ROD' LABORATORY STOOL CHAIR! VIBRATION ANALYSIS OF CENTRIFUGAL FAN፤ BLADE FUSE፣ የተለያዩ አልባሳት, ጫማዎችና ሌሎች PERFUME HAIR CLIPPER, VACUUM FLASK & OTHER SHITI WITH SCARVE, CHAWING GUM & OTHER LADY SKIRT LADY TROUSER, LADY TIGHT & OTHER AS TOYOTA OIL FILTER እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 መመልከት ይቻላል።

2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3) ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበት ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFECE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።

4) የጨረታ ማስታወቂው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10) ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-9094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡45 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-21 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian's Customs Commission Modjo Branch Office
  • Bid bond: 300,000.00 (ሦስት መቶ ሽህ ብር)
  • Published: Jul 16, 2026
  • Posted at: 2026-07-16T07:59:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders