የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን ያልተጠረበ ወይም ለግንባታ ያልተዘጋጀ የቦርደር ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የድንጋይ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ኮተቤ ሰዓሊተምህረት አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን ያልተጠረበ ወይም ለግንባታ ያልተዘጋጀ የቦርደር ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ያልተጠረበ ወይም ለግንባታ ያልተዘጋጀ ቦርደር ድንጋይ መግዛት የሚፈልግ (ገዥ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማየት መግዛት ይችላል፡-

  1. የአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ጨምሮ ብር 4,000.00 (አራት ሺህ · ብር) ስለሆነ ገዥው ቢያንስ 05 /አምስት/ ቢያጆ እና ከዛ በላይ ብዛት መግዛት ይችላል።
  2. ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ በብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) የ05 /አምስት/ እና ከዛ በላይ ቢያጆ አጠቃላይ ዋጋ በEEU-UEAP A/C No 1000-604742556 ገቢ በማድረግ የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንፃ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ደረሰኝ ማስቆረጥ ይችላሉ።
  3. ገዥዎች የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ፤ ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ኮተቤ አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ድንጋዩን የሚጭን መኪና በማቅረብ ድንጋዩን አስጭነው መውሰድ ይችላሉ።
  4. ግዥውን የፈጸመ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ክፍያ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ የከፈለበትን ድንጋዮች ማንሳት አለበት። በእነዚህ ቀናቶች ውስጥ ያላነሳ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ገንዘቡ የማይመለስ መሆኑን እናሳውቃለን።
  5. ድንጋዩን በተጫራች መኪና ላይ የመጫን ኃላፍነት የሻጭ ነው።
  6. ድንጋዩን የሚጭን መኪና የማቅረብ ኃላፍነት የገዥ ነው ።
  7. ገዥ መግዛት የሚችለው ዝቅተኛው የቢያጆ መጠን 05/አምስት/ ነው።
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-126-3153 መደወል ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-31
  • Publishing entity: Ethiopia Electric Utility Project Portfolio Management Bureau
  • Published: Jul 16, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders