የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ፎርስ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ፎርስ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከ10/11/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለግልፅ ጨረታ በመሳተፍ ተሽከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ ከአምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካረ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  5. ተሽከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  9. ተጫራቹ ተሸከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
  10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከ10/11/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ14/11/2018 ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤

NB-

አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።

የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለመጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
  • Bid bond: 5%
  • Published: Jul 16, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders