የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች -
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሀምሌ 9/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 16/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3) ማንኛውም ተጫራች ከሀምሌ 9 እስከ ሀምሌ 16, 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ እና ሜክሲኮ በሚገኘው ጋራዥ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።
4) ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሀምሌ 16 ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6) ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው::
7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 047 4668 ወይም 251 91 156 9913 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-07-23 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Refugee and Returnee Service
- Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 16, 2026
- Posted at: 2026-07-16T08:53:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.