የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያየ መጠን ያላቸው ጄኔሬተሮች፣ የውሃ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያለፉ መጻህፍት፣ የነዳጅ መቅጃ፣ የልብስ ስፌት መኪና እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የዕቃዎች ሸያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያየ መጠን ያላቸው ጄኔሬተሮች፣ የውሃ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የአገልግሎት ጊዜያቸዉ ያለፉ መጻህፍት፣ የነዳጅ መቅጃ፣ የልብስ ስፌት መኪና እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋምቤላ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሐምሌ 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugee and Returnee Service/ በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ማንኛውም ተጫራች ከሐምሌ 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።

4. ጨረታው ጋምቤላ በሚገኘው የአግልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሀምሌ 24/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል።

5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ዉስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6. ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘዉ ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለዉን አማራጭ የመዉሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251911278481 ወይም +251910464496 ይቻላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-31
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-31 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 17, 2026
  • Posted at: 2026-07-17T08:09:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders