አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከ ሐምሌ 2025 እሰከ ሰኔ 30,2026 ድረስ ለ1 ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪውን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈለግ ሲሆን ከአሸናፊው የኦዲት ድርጅት ጋር ለ3 ዓመታት ውል ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በዳግም ምዝገባ ቁጥር 1544 ተመዝግቦ የሚገኝ በኢትዮጵያ ነዋሪዎች ድርጅት በማዕከላዊ አትዮጵያ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በተለያዩ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ስለሆነም እ.ኤ.አ ከ ሐምሌ 2025 እሰከ ሰኔ 30,2026 ድረስ ለ1 ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪውን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈለግ ሲሆን ከአሸናፊው የኦዲት ድርጅት ጋር ለ3 ዓመታት ውል ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛውም የአዲት ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች መሟላት የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የኦዲተርነት የፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲት መ/ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- ካሁን በፊት ባከናወኑዋቸው የኦዲት ስራዎች የመልካም ስራ አፈጻጸም ድርጅቶች ሰለመስራታቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች መረጃውን እና የምትሰሩበትን ዋጋ ዝርዝር በፖስታ አሽጎ ቢሮአችን ድረስ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ጀርባ በሚገኘዉ አጋር ድርጅታችን ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ዓመታዊ በጀት 66,397,710.00 (ስልሳ ስድስት ሚሊያን ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አስር ብር) ሲሆን
- የቦክስ ፋይል ብዛት 45 (አርባ አምስት) ብቻ ነው።
- የምንጠቀመው የሂሳብ ሲስተም ኢብሳስ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
የኦዲት ድርጅቱ ለሚልከው ባለሙያ ማንኛውንም የምግብ የአልጋ፤ የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
አድራሻ ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ቅበት ከተማ ከቦዜ ት/ቤት ፊት ለፊት (ከአዲስ አበባ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ ከቡታጅራ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ) ስልክ ቁፕር 09 13 38 14 37/ 09 16 04 03 27
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Publishing entity: Aynage Children and Family Development Organization
- Published: Jul 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.