በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ሃራጅ ጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡
ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን;
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታው አይነት |
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት |
ስልክ ቁጥር |
|
1 |
ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች |
ሃራጅ
|
10/11/2018 |
15/11/2018 |
4:00
|
8:00
|
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
2 |
ተሸከርካሪ |
ሃራጅ |
10/11/2018 |
15/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
|
3 |
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች |
ሃራጅ |
10/11/2018 |
15/11/2018 |
4:00 |
8:00 |
022 111 8429/ 022 211 8925 |
5. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
6. በጨረታው ላይ የወጡት ሞተር ሳይክሎች እና ተሽከርካሪ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ መጫረት ይችላል።
7. በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 01, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 331,200.00፣ ለምድብ 02, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 28,000.00 ፣ ለምድብ 03 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 193,700.00፣ ለምድብ 04, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 768,400.00፣ ለምድብ 05, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 539,000.00፣ ለምድብ 06, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 1,406,400.00፣ ለምድብ 07, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 934,000.00፣ ለምድብ 08, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 781,500.00፣ ለምድብ 9, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 129,400.00፣ ለምድብ 10, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 186,500.00 ፣ ለምድብ 11 ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 684,000.00፣ ለምድብ 12, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 102,700.00፣ ለምድብ 13, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 618,700.00፣ ለምድብ 14, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 109,500.00፣ ለምድብ 15, ተሽከርካሪ ብር 216,710.00፣ ለምድብ 16, ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00 እና ለምድብ 17, ሞተር ሳይክሎች 10,000.00 (Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
8. በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም ተሽከርካሪው በከልቻ ግቢ መጋዘን ቁጥር 10 ውስጥ ሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 /ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ሰዓት መሰረት መጫረት ይቻላል።
9. በሃራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል ።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት) የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
13. ከላይ በተ/ቁ 11 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
14. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች
022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-22
- Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jul 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.