በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገ/ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ለመግዛት ይፈልጋል

  1. የምግብ እህል ጨረታ ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ 5000 ብር
  2. የመኪና ዘይታ ዘይት ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 16000 ብር
  3. የመኪና ጎማ ጨረታ ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር
  4. የመኪና ጥገና ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ 10000 ብር
  5. የመኪና መለዋወጫ ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር
  6. የኤሌክትሮኒክስ/ኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች ጥገና ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ 5000 ብር
  7. የስፖርት ዕቃዎች መገልገያ ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ 5000 ብር
  8. የስፖርት አልባሳትና ጫማዎች ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ 5000

ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10/11/2018 ዓ.ም እሰከ 25/11/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

2. በጨረታው የሚሣተፍ በዘመኑ የታደሠ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፉይ መለያ ቁጥር / ቲን ነምበር/ የቫት ተመዝጋቢ/ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃውን አይይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ስዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም።

4. ተጫራቾች የሞሉበትን የጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙበትንም ደረሠኝ ከሆነ ፎቶ ኮፒ አድርገውማቅረብ አለባቸው፤ CPO ከሆነ ዋናውን ማቅረብ አለባቸው።

5. የንግድ ፍቃድና የመሣሠሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፤ በፖስታው ላይና እንዲሁም በጨረታ ዋጋ መሙያ የጨረታ ሠነድ ላይ የተጫራቾች ስምና ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።

6. በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

7. ተጫራቾች አሽናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ 10% በማሲያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሠጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መሠረት አሸናፊነቱ በተገለፀው በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

9. ለአሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን ብር ከአሽናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።

10. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት፤ ሁሉንም ካልሞሉ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።

11. ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የህዝብ በዓላት፣ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀናትበተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

12. የጨረታ ሰነዱን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት ብር 300 / ሦሥት መቶ ብር/ በማይመለስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።

13. ሂሳብ የሚከፈለው አሸናፊው ተጫራች በውሉ መሰረት እቃዎቹን ሲያጠናቅቅ ክፍያውን ይወስዳል።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

15. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጠል መ/ቤቱ በሚያዋጣዉ ነው።

16. የስፖርት ትጥቅ ፣ ኳስ እንዲሁም የደንብ ልብሶች እና ሌሎች ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ሣምኘሉን በማየት ዋጋ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው።

17. ከ200,000 ሺህ ብር በላይ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።

18. ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 6851461/0106 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገ/ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10/11/2018 ዓ.ም እሰከ 25/11/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-03 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 10/11/2018 ዓ.ም እሰከ 25/11/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Menze Gera Medere Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 17, 2026
  • Posted at: 2026-07-17T09:00:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders