ወደ እናት ፍቅር የበጎ አድራጎት ማህበር አመታዊ የሒሳብ እንቅስቃሴ ማስመርመር ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

ወደ እናት ፍቅር የበጎ አድራጎት ማህበር ትኩረቱን የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንን እና የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ላይ አድርጎ የሚሰራና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን እ.ኢ.አ የ2018 አመታዊ የሒሳብ እንቅስቃሴ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ተቀባይነት ባላቸው ኢትዮጵያ ኦዲተሮች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ማስመርመር ይፈልጋል።

1. የታደሰ የስራ ፍቃድ ያለው እና አስፈላጊውን የመንግስት ግብር የከፈለ፤

2. ከዚህ በፊት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሒሳብ ኦዲት የማድረግ ልምድ ያለው፤ 

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፡፡ በዚህም መሰረትለምትሰጡት አገልግሎት የምትጠይቁትን የገንዘብ መጠን (ተ.እ.ታክስን ጨምሮ) እንዲሁም የአመቱን የሒሳብ ምርመራ ጨርሳችሁ የምታስረክቡትን ቀን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በታሸገ ፖስታ በድርጅርቱ ቢሮ ማቅረብ ትችላላችሁ።

 አድራሻ፡- አዳማ በዳቱ ወረዳ መብራት ሃይል ምንጭ የገብያ ማዓክስ 5ኛ ፎቅ ቢሮ  ቁጥር 5-06 ያገኙናል።
ለበለጠ መረጃ፡- 09 10 39 47 72/ 09 27 75 89 30 ይደውሉልን
ወደ እናት ፍቅር የበጎ አድራጎት ማኀበር 


Tender details

  • Deadline: 2026-07-27
  • Publishing entity: ወደ እናት ፍቅር የበጎ አድራጎት ማህበር
  • Published: Jul 18, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders