በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት ለባቲ ከ/አስ ለሁሉም ሴክተር ጽ/ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ማለትም
- ሎት 1 የላንድ ከሮዘር እና የሀይላክስ ኩን 25 የመኪና ጎማዎች እና ከለማዳሪያ፣
- ሎት 2. ባትሪ፣ ፊልትሮዎች እና ፈሬን ሸራወችን፣
- ሎት 3 . የባጃጅ መለዋወጫች፣
- ሎት4 የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸው በጀርባው የሚገልፅ ካለው ኮፒ አድርገው ያያይዙ
2. የግብር መለያ ቁጥር ወይም TIN NO ተመዝጋቢ የሆነ፡
3. ተጫራቾች እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁ, 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ማቅረብ የሚችል፡
5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁ.6 ከዋና ገ/ያዥ ላይ መግዛት ይችላሉ። የሚወዳደሩበት ሰነድ የያዘው ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩት ቁርጥ ዋጋ
ለሎት 1 የላንድ ከሮዘር እና የሀይላክስ ኩን 25 የመኪና ጎማዎች እና ከለማዳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር)፣
ሎት 2.ባትሪ ፊልትሮወች እና ፈሬን ሸራወችን 6,000 (ስድስት ሺ ብር)፣
ሎት 3, የባጃጅ መለዋወጫዎች 6,500 (ስድስት ሺ አምስት መቶ ብር)፣
ሎት4 የሞተር ሳይከል መለዋወጫዎች 10,000 (አስር ሺ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ወይም cpo ወይም ቢድ ቦንድ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባቲ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት በመሂ1 ገቢ አድርጎ ከዋና ጨረታ ሰነድ ጋር ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ አለባቸው፣በእጅ cpo ወይም ጥሬ ገንዘብ ይዞ መቅረብ አይቻልም።
7. ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን ማለትም ከ11/11/2018 እስከ 25/11/2018 የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ከጽ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
8. ይህ ግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ላይ በ26/11/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሁሉም ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን ሎት 1 እና ሎት 2 ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት፣ ሎት 3 እና ሎት 4 ከጠዋቱ 5፡00 ሰአት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ሳይገኙ ቢቀሩ ለጨረታውን ከመክፈትም ሆነ በጨረታውን ሂደት ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ናቸው።
9. ጨረታውን መ/ቤቱ በሎት ድምር ማወዳደር እንደሚችል ታውቆ በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ሁሉ ዋጋቸው መሟላት አለባቸው። ሳይሞሉ የቀሩ ካሉ ከጨረታ ውጭ ውድቅ ይደረጋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በባቲ ከ/አስ/ ስር ባሉት 4 ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. በባለሙያ መታየት ያለባቸው እቃዎችን ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ባለሙያ አረጋግጠን የምንረከብ መሆኑን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው።
12. የእቃ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በመጠቀም በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ መሰረት መሞላት ይኖርበታል፤ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን | ከተቀየረ ውድቅ ይደረጋል እንዲሁም ስርዝ ድልዝ / በሌለበት ሁኔታ ተለይቶ በዝርዝር በመሙላት የድርጅቱን ስም በመፃፍ በመፈረምና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናል ይደረጋል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህ ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለማወዳደር እና ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን።
14. መ/ቤቱ 20% የመቀነስ እና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታ ሳጥኑ በሚቀጥለው በቀጣዩ የስራ ቀን ታሽጎ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 19 24 12 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ባቲ ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-03
- Publishing entity: Bati City Administration FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 18, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.