አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያገለገለ ጎማ፣ ፊልትሮ፣ አየር ማጣሪያ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ያገ/ን/ሽ/ግጨ/007/2018

አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች ለአንድ አመት በሚቆይ ውል በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

.

የሚሽጠው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

የጨረታ ሰነድ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ሎት 1-ያገለገለ ጎማ

 

በሚወዳደሩበት ሎት የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሐምሌ 28/2018 . ሰዓት 800

ሐምሌ 28/2018 . ሰዓት 830

 

2

ሎት2-ፊልትሮ፣ አየር ማጣሪያ

በሚወዳደሩበት ሎት የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

ሐምሌ 28/2018 . ሰዓት 800

ሐምሌ 28/2018 . ሰዓት 830

 

ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለበት።

2. ተጫራቾች 22 በሚገኘው ኢየሩስ ህንፃ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ደርጅት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡oo ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በሚገኙበት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ፣ የካ ቅ/ጽ/ቤት፣ ሰሚት ቅ/ፅ/ቤት፣ ሸጎሌ ቅ/ጽ/ቤት እና መካኒሳ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ። ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት የሎቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።

4. የጨረታ ሳጥኑ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሃያ ሁለት ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል።

5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 666-3367 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-04 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Bus Service Enterprise
  • Bid bond: በእያንዳንዱ ሎት 10% (አስር በመቶ)
  • Bid document price: 700.00 (ሰባት መቶ ብር)
  • Published: Jul 19, 2026
  • Posted at: 2026-07-20T07:36:40.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders