በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዕቃዎች ለመሽጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 42/2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ
- የሞተርሳይከል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፤ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የመገናኛ መሳሪያዎች፤
- ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ነዳጅ፤
- ምግብ ነክ ዕቃዎች ፤የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የግልጽ እና ሃራጅ ጨረታ ሰነድ በተሌግራም አካውንት የሚላክላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ. ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C..P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት C.RO ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡ ሀ. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡45
- Bid opening: 2026-07-27 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Moyale Customs Branch Office
- Bid bond: በግልፅ ጨረታው 5% እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል
- Bid document price: ለእያንዳንዱ 100.00 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jul 19, 2026
- Posted at: 2026-07-20T08:07:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.