አዋሽ ባንክ አ.ማ በፅህፈት ሥራ ላይ ላልተሰማሩ የባንኩ ሰራተኞች የደንብ ልብስ ማሰፋት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RE-AB/002/2026-27.
1. አዋሽ ባንክ አ.ማ በፅህፈት ሥራ ላይ ላልተሰማሩ የባንኩ ሰራተኞች የደንብ ልብስ ማሰፋት ይፈልጋል።
2. በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና የመንግስት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው።
|
ተ/ቁ |
መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1 |
የሴት ኮት እና ሱሪ ሙሉ ልብስ ስፌት በሙሉ ገበር |
ሙሉ ልብስ
|
326
|
የገበር ጨርቅ ከተጫራቾች ይሆናል
|
|
2 |
የሴት ኮት እና ጉርድ ቀሚስ ስፌት በሙሉ ገበር |
|||
|
3 |
የወንድ ሙሉ ልብስ ስፌት ኮት እና ሱሪ በሙሉ ገበር |
444 |
3. በተጫራቾች የሚቀርበዉ የስፌት ዋጋ በደንብ ሊነበብ በሚችል የእጅ ፅሁፍ ወይም በኮምፒዩተር ተፅፎ መቅረብ ይኖርበታል:: ስርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉጪ ይሆናል።
4. ተጫራቾች የተዘጋጀዉን ሰነድ ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6:00 ሠዓት ከሰዓት ከ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01540000544500 በየትኛዉም የባንኩ ቅርንጫፍ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ገቢ በማድረግ አዋሽ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ 12ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ገዥ ዋና ክፍል ቢሮ በአካል ቀርቦ መዉሰድ ይችላሉ።
5. በተጫራቾች የሚቀርበዉ ዋጋ የእጅ እና የገበር ዋጋን ያካተተ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ኦርጂናል እና ኮፒ የቴክኒካል እና የዋጋ ሠነዶች ለየብቻ (ለየቅል) በታሸገ ኤንቨሎፕ በዕለቱ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ አዋሽ ባንክ ዋና መ/ቤት ህንፃ 12ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ገዥ ዋና ክፍል ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በእለቱ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ 8:30 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር 4 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል።
8. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን መስፈርት ያላሟሉ ተጫራቾች ከጨረታ ዉጪ ይሆናሉ።
9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57-11-07 ወይም 0115-57-00-84 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዋሽ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-30 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Awash Bank Share Company
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jul 19, 2026
- Posted at: 2026-07-20T08:18:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.