የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን፣ ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን፣ ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች፣ ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን እና የደንብ ልብሶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- የፅህፈት መሳሪያዎች
- የፅዳት እቃዎች
- የኤሌክትሮንክስ እቃዎች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎችን
- ባጃጅና ሞተር ሳይክሎችን
- ለኤሌክትሪክና ለውሃ ዝርጋታ የሚያገለግሉ እቃዎች
- ለቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚያገለግሉ እቃዎችን
- የደንብ ልብሶችን
በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና፣ ጨረታ ላይ እንድሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 3000.00( ሦስት ሺህ ብር) በመክፈል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO ብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- አሽናፊው ያሸነፈበትን የእቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የእቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለጸለት ያሸነፈበትን እቃ ብዛት አባዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ለሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
ስልክ ቁጥር፡-0221161644/2239 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-06 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Mojo City F/E/D/Bureau
- Bid bond: 60,000.00 ብር
- Bid document price: 3000.00 ብር
- Published: Jul 19, 2026
- Posted at: 2026-07-20T09:36:39.000Z
Documents
Categories
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureSpare Parts and Car Decoration MaterialsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseHand Tools and Workshop EquipmentMechanicalTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsInstallation, Maintenance and Other Engineering ServicesMaterialsEducation and TrainingWater Pipes and FittingsConstruction and Water WorksWater ConstructionSanitary and CeramicsPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsBuilding and Finishing MaterialsAmharic2merkatoMojo City F/E/D/BureauOromia
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.