Building and Finishing Materials
የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ጥቅል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ጥቅል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒዩተር ዕቃዎች፣
- የመኪና ዕቃዎች፣
- የግብርና ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የፅህፈት መሣሪያ፣
- ጨርቃ ጨርቅ፣
- የጋርመንት ዕቃዎች፣
- የእንስሳት መኖ፣
- የእንስሳት መደኃኒት፣
- የሞባይል ዕቃዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፤ ለመወዳደር የምትፈልጉ የመወዳደሪያ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 1 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ በመውሰድ የምትሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 1 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን እንድታስገቡ እየገለጽን፡-
1. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
2. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡ ፡ በእለቱ ካልተገኙ ግን ጨረታው በኮሚቴ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን በህዝብ በአል ወይም በእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለህንጻ መሳሪያ 5,000 ብር፣ የጨርቃ ጨርቅ እቃዎች 1,000 ብር፣ የኤሌክትሮኒክስና የኮምፒዉተር ዕቃዎች 5,000 ብር፣ የእንስሳት መኖ 2,000 ብር፣ የእንስሳት መድኃኒት 2,000 ብር፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 2,000 ብር፣ የመኪና እቃዎች 5,000 ብር፣ የግብርና ዕቃዎች 2,000 ብር፣ የፅህፈት መሣሪያ 2,000 ብር፣ የጋርመንት ዕቃዎች 2,000 ብር፣ የሞባይል ዕቃዎች 1,000 ብር፣ የፅዳት ዕቃዎች 1,000 ብር ፣በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ከጨረታው ፖስታ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የስራ ፈቃድ የታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከመጫረቻ ፖስታው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የመጫራቻቸው ጠቅላላ ዋጋ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው እስፔስፊኬሽን ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም እንዲሁም ስነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ መመሪያ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፡፡
8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት (በድምር) ዋጋ በሞሉት ነዉ፡፡
10. ለበለጠ መረጃ 058 771 26 32፣058 771 16 93 ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-18
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ
- Bid opening: 2026-11-19 10:00
- Bid opening (note): በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debre Markos Poly Technique College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T14:05:34.000Z
- Source: Qelal Tenders