Building and Finishing Materials

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባሕር ዳር አባይ ማዶ ቀበሌ ህዳር 11 ከኮባል ኢንዱስትሪ ጎን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች

  • ሎት 1. የህንፃ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2. የህክምና እቃዎች፣
  • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 5. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 6. ፈርኒቸር እቃዎች፣
  • ሎት 7. ብትን ጨርቅ፣
  • ሎት 8. የተዘጋጁ ልብሶች፣
  • ሎት 9. ጫማዎች፣
  • ሎት 10. የመኪና መለዋወጫዎች፣
  • ሎት 11. የመኪና ዘይትና ቅባቶች እንዲሁም
  • ሎት 12. የክራንች ቲፕስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  2.  የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች የዋጋዉን ጠቅላላ አንድ በመቶ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ዋጋቸዉ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  5. ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋዉን 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡
  6. አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስረከቢያ የዉሉን ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10.  የእቃዎችን አይነት /ሞዴል /ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ11ኛዉ ቀን 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ ይሆናል፡፡
  14. ማዕከሉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. በማንኛውም ግዥ ለእቃ ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች ለአቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3 በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82 /058 820 97 84 በመደወል ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ11ኛዉ ቀን 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-19 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ11ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bahir Dar Disables Rehabiltation Service Center
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T13:15:07.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders