በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የቧንቧ እና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሴ/መ/ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የቧንቧ እና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎችን በዋን ዋሽ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።

3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ።

4 የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮቁጥር4 ማግኘት ይቻላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ ለሚወዳደሩበት ለቧንቧና የውሀ መገጣጠሚያ እቃዎች 20,000 ሀያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና/ኦሪጂናል እና ቅጂኮፒ/ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 28/11/2018ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላፊ ክፍል በቢሮ ቁጥር1 በቀን 28/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።

11.ተጫራቹ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ ስፕስኬሽን በማሟላት ዕቃው የተመረተበትን ሀገር፣ የአምራቹን ስም የዕቃውን ሞዴልና የመሳሰሉትን አካቶ መሙላት ይጠበቅበታል።

12. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ድምር ዋጋ ወይም በነጠላ ዋጋ የሚያወዳድር መሆኑን ይገልፃል።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 022 472 0080 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-08-04 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jul 20, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T07:02:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders