በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የህክምና እቃ መድኃኒትና ሬጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001 /19

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተቀመጠው መድኃኒትና እሬጀንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተቁ

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ

1

1

የህክምና እቃ መድኃኒትና ሬጀንቶች

40,000

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ቲን ቁጥር ያላቸው።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. የገቢዎች ክሊራንስ የጨረታ መሳተፊያ ያለው።

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 48 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 48 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለውን የስራ ቀን በመጠቀም በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ዘግይቶ የሚመጣ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም።

10. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን መድኃኒትና ሬጀንቶች በራሱ ትራንስፖርት የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት።

13. ጤና ጣቢያው ለጨረታ ካቀረበው እቃ 20% ድረስ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀን ነው።

16. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማሰራት አለባቸው።

17. በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ኦርጅናል መሀተም ሊኖር ይገባል።

18. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት ማካተት አለባቸው።

19. ተጫራቾች የተፈለገውን እቃ ሳይሰርዙ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው መድኃኒት /እሬጀንት ዋጋ ብቻ በዋጋ መሙያ ላይ መሙላት አለባቸው ይህን ያላደረገ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል።

20. ከጨረታ ሰነድ ውጭ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

21. የጨረታ መስከበሪያ በ ወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ስም ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

አድራሻ፡- ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ፊጋ መብራቱ ጋር እንደደረሱ ወደ ግራ
30 ሜትር ገባ ብሎ።
ስልክ፡-0118593464
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና


Tender details

  • Deadline: 2026-07-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-31 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ጠዋት 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Woreda 08 Amorawe Memorial Health Center
  • Buyer address: ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወ/8 አሞ/ጤ/ጣቢያ ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ፊጋ መብራት ጋር እንደደረሱ ወደ ግራ 30 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: 40,000 (አርባ ሺ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jul 21, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T07:32:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders