ለጉራጌ ዞን አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት እያሰራ ያለው አዲሱ B+G+9 ህንጻ ግንባታው እየተጠናቀቀ ስለሆነ ለዚሁ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018-19
ለጉራጌ ዞን አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት እያሰራ ያለው አዲሱ B+G+9 ህንጻ ግንባታው እየተጠናቀቀ ስለሆነ ለዚሁ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሰረት ፡-
1. በመስኩ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ የሙያ ፍቃድ ያደሳችሁ ለመሆናችሁ መረጃ የምታቀርቡ፣
2. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣
3. በጨረታ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መቅረብ አለባቸው ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 / አንድ ሺህ ብር / በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በተናጠል በታሸገ ፖስታ 1 ቴክኒካል ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በጥንቃቄ በተናጠል በታሸገ ፖስታ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ እናት ፖስታ ለጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የግዥ መመሪያ በሚፈቅደው ዋስትና ቢድ ቦንድ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ከሚያቀርቡት ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
9. ጨረታው በ21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ላይ በጉራጌ ዞን ፋይናስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ ፡
- በአፈጻጸማቸው ምክንያት የ3ተኛ ዙር ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተወዳዳሪዎች መወዳደር አይችሉም።
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-330-0112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በማዕ/ኢ/ክ/መ/ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Publishing entity: Gurage Zone Finance Office
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Jul 22, 2026
- Posted at: 2026-07-22T08:52:18.000Z
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.