ኤስ አይ ኤም ኢትዮጵያ ከታክስ ነፃ የገቡና ከ30 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሰባት (7) አውቶሞቢሎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኤስ አይ ኤም ኢትዮጵያ ከታክስ ነፃ የገቡና ከ30 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሰባት (7) አውቶሞቢሎች፣ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።
የጨረታ ሰነድ ስለመግዛት፡- ተጫራቾች ኦርጅናል ማህተም ያለበትን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 /ሰባት መቶ ብር/ በመክፈል ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል አካባቢ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ጎን በሚገኘው የኤስ አይ ኤም ቅጥር ግቢ በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ማለትም ከእሮብ ሀምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከ2፡30-10፡00 ሰዓት) የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ድርጅታችን በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ሊገዙበት የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ማለትም እሮብ ሀምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አርብ ነሃሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል አካባቢ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ጎን በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በመምጣት ማስገባት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ /20%/ በሶሳይቲ ፎር ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪስ /ኤስ አይ ኤም/ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ነሃሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 በድርጅቱ ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን፤ አሽናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን /ሲፒኦ/ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በአስር ቀናት ውስጥ ከፍሎ ንብረቱን ማንሳት ግዴታ አለባቸው።
5. የጨረታው አሸናፊ ከፍሎ የማይወስድ ከሆነ ለጨረታው ማስከበሪያ /ቢድ ቢንድ/ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡።
6. የጨረታው አሸናፊ ከስም ዝውውር ጋር የተያያዙ የቦሎ፣ የቀረጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችንና ማንኛውንም የተሽከርካሪ ነክ ተዛማጅ ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊ ይሸፍናል ይከፍላል/።
7. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊ ሙሉ ክፍያውን እንደፈፀሙ የሚመለስላቸው ይሆናል።
8. የጨረታው ሰነድ ሽያጭ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐሙስ ነሃሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ብቻ የሚቆይ ይሆናል።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ዋና ቢሮ፤ አዲስ አበባ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል አካባቢ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን ጎን
ስልክ ቁጥር፡- 011 550 3899 / 09 35 40 16 14
ኤስ አይ ኤም ኢትዮጵያ/ ሶሳይቲ ፎር ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪስ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-14
- Publishing entity: Societies For International Ministries (SIM Ethiopia)
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 700.00 ብር
- Published: Jul 22, 2026
- Posted at: 2026-07-22T08:57:27.000Z
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.