Disposal, scrap and surplus sales

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተለያዩ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

  1. የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው የአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ካምፓስ አካባቢ ባለው ቅጥር ግቢ እና መጋዘን የሚገኙትን  የተለያዩ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና  ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሀምሌ 15/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከሀምሌ 15 እስከ ሀምሌ 27/ 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል።
  4. ጨረታው አሶሳ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሀምሌ 27 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
  7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251952823095 ወይም 0577752465 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

አድራሻ፦ አሶሳ ከተማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አካባቢ ውሃና ፍሳሽ ጽ/ቤት ጎን

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid opening: 2026-08-03 14:00
  • Region: Beneshangul Gumuz
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 22, 2026)
  • Posted at: 2026-07-22T09:43:24.000Z
← Back to all tenders