የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/01/2019

1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/01/2019 የሚል ምልክት በማድረግ (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስምየተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ህዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ይከፈታል።

7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 40 11 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-03 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jul 23, 2026
  • Posted at: 2026-07-23T07:42:05.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders