የጭነት መኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሽፈራው ተስፋዬ እና የፍ/ባለዕዳ ለንጮ ለታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/6798 በ30/11/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/07565 በ04/04/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 3-35704ኢቲ UD-Nissan ገልባጭ የጭነት መኪና የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,714,875 ( አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አምስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-11 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 23, 2026
- Posted at: 2026-07-23T07:53:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.