External audit and assurance
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማኅበር ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት ሂሳቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የኦዲት ሥራ ባለሙያ ማስታወቂያ፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማኅበር ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ተከታታይ የበጀት ዓመታት ሂሳቡን ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ የኦዲት ተቋማት አወዳድሮ አሸናፊውን መምረጥ ይፈልጋል።
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፤
1) በአዋጅ ቁጥር 847/2006 አንቀጽ 18 መሠረት የኦዲት ሙያ ማረጋገጫ ያለውና በመንግሥት የተመዘገበ፣
2) በኦዲት ሥራ በቂ ልምድ ያለው፣
3) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
4) ከአሁን በፊት ኦዲት ያደረጋቸውን ድርጅቶች ዝርዝር ማቅረብ የሚችል፣
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የምትሠሩበትን ዋጋ እና ሥራውን ሠርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ደረጃችሁን እና ሕጋዊነታችሁን የሚገልጽ ማስረጃችሁን በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
አድራሻ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መሥሪያ ቤት ግቢ፣
የስልክ ቁጥር፣ 011 517-8283 / 011 517-8753
ሞባይል 09 37-92-96-03
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-10 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጡረተኞች ማህበር
- Published on: Addis Zemen (Jul 24, 2026)
- Posted at: 2026-07-24T07:46:46.000Z